Channel: AmharicTube
Category: Entertainment
Description: እናት ባንክ የራይድ ትራንስፖርትን መስጠት ለሚፈልጉ አሽከርካሪዎች የመኪና ዋጋውን 30% በመቆጠብ መኪና የሚገዙበት ብድር አመቻችቻለው አለ ። እናት ባንክ ከሃብሪድ ዲዛይን - ራይድ ጋር በስትራቴጂያዊ አጋርነት እና በትብብር አብሮ ለስራት የግባቢያ ስምምነት ዛሬ ተፈራሟል። በስምንነቱ መሰረት " ራዕይ " በተባለው የብድር አይነት በራይድ ውስጥ ተመዝግበው የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎች የመኪና ዋጋውን 30 በመቶውን በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ በመቆጠብ መኪና መግዛት የሚችሉ ሲሆን ቀሪ ክፍያውን ደግሞ በአምስት አመት ጊዜ ውስጥ ያጠናቃሉ ተብሏል። "እፎይታ" በተባለው ይህ የብድር አልግሎት ተጠቃሚ የሚሆኑ የራይድ አሽከርካሪዎች ለዓመታዊ ግብር ክፍያ ፣ ለመኪና ገገና እና ተያያዥ ወጪዎች ለመሸፈን የሚውል ሲሆን አሽክካሪዎች በትንሹ ለሦስት ወር የእናት ባንክ ደንበኛ በመሆን ለሶስት ወር በቋሚነት የሚቆጠብ ከሆነ እስከ 10, 000 ብር ደረስ ብድር ማግኘት ይችላሉ ተብሏል። "ደራሽ "በተባለው የብድር አገልግሎት የሚጠቀሙ የራይድ አሽከርካሪዎች ለተዘዋዋሪ የሥራ ማስኪያጃ የሚያውሉት እስከ አንድ ሺ ብር የሚደርስ ብድር ነው። ይህ የብድር አገልግሎት ሽከካሪዎቹ የራይድ የትራንስፓርት አገልግሎት በሚሰጡበት ወቅት የሚቀሙበት ብድር ሲሆን ፣ ምንም ዓይነት የወለድ ምጣኔ የማይታሰብበትና ለተወሰደው ብድር በቀን አንድ ብር ብቻ የአገልግሎት ክፍያ የሚታሰብበት ነው :: Subscribe to our channel Amharic Tube and enjoy Ethiopian daily news, Ethiopian movies, Ethiopian drama and Ethiopian comedy